የሰንበት ትምህርት ቤታችን ራዕይ



https://youtu.be/eFpAp1urXXY

፩. የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት ሃይማኖት ከምግባር አጣምረው እንዲይዙ ማስቻል ነው::
፪. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓትተጠብቆ ሳይበረዝ እና ሳይለወጥ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ፡፡
፫. ማንኛውም የቤተክርስቲያኒቱ ተከታይ የሆነ ክርስቲያን ሁሉ ሃይማኖቱን እና የሃይማኖቱን ሥርዓት በውል እንዲያውቅ ማድረግ
፬. ሕፃናት እንዲሁም ወጣቶች በሰ/ት/ቤቱ ተደራጅተው እየተማሩ የቤተክርስቲያንንም ሆነ የሀገርን ታሪክ በሚገባ አውቀው በነገረ-መለኮት እና ሃይማኖታዊ ትምህርት ብስለት እንዲያገኙ የነገዋን ቤተክርስቲያንና ሀገርን በኃላፊነት ለመረከብ ብቁዎች እንዲሆኑ ማድረግ
፭. ህፃናትና ወጣቶች የቤተክርስቲያንን ሕግና ሥርዓት (ቃለ እግዚአብሔር) ተምረው ወላጆቻቸውን እና ታላላቆቻቸውን አክባሪዎች እንዲሆኑ፤ በአጠቃላይ በሃይማኖት እና በሥነ-ምግባር ታንጸው እንዲያድጉና ለሀገርና ለወገን መልካም ዜጎች እንዲሆኑ ማድረግ
፯. የሰ/ት/ቤቱ አባላት ያላቸውን ሙያ፤ እውቀት፤ ገንዘብና ጉልበት ለቤተክርስቲያኒቱ እንዲያበረክቱ ማድረግ ነው፡፡